|
የማሕበራዊ አገልግሎት በርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርሰቲያን ዘወትር ከሚሰጠው የተሟላ መንፈሳዊ አገልግሎት በተጨማሪ፣ ሕብረተሰቡን ሊጠቅሙ የሚችሉ የተለያዩ ማሕበራዊ አገልግሎቶች ይሰጣሉ። በዚህ የማሕበራዊ አገልሎት ዘርፍ ከትውልድ ሀገራቸው ርቀው የሚኖሩት ምዕመናን ከቤተ ክርሰቲያኒቱ ከሚያገኟቸው ማሕበራዊ አገልግሎቶች፡
ይህ የማሕበራዊ አገልግሎት የማሕበረሰብ ሳይንስ፣ የሳይኮሎጅ እና የቴክኖሎጅ ባለሙያ በሆኑ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት፣ በተጋባዥ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች፣ አሜሪካ አገር በሚገኙ የተለያዩ በበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና በሌሎችም ይሰጣል።
ቤተ ክርሰቲያናችን ሁሉንም አይነት የሕብረተሰብ ክፍል ያካተተ ምዕመናን የሚገኝባት፣ ለሕዝብ ማማለሻ ትራንስፖርት አመች የሆነ አማካይ ቦታ ላይ የምትገኝ፣ በቂ የሆነ የመኪና ማቆሚያ ያላት፣ ለስለጠና የሚሆኑ በቂ ክፍሎች ያሏት፣ መለስተኛ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ያላት፣ ሳምንቱን በሙሉ ክፍት የሆነች እና አስተዳደራዊ መዋቅሯ ለበጎ ፈቃድ አገልጋዮች ምቹ የሆነች በመሆኗ፤ ሕብረተሰባቸውን በነጻ ለማገለገል ፈቃደኛ ለሆኑ ባለሙያዎች እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ሁሉ ሁኔታዎች የተመቻቹ ናቸው።
በዚህ አገልሎት በመሳተፍ ሕብረተሰባችሁን በነጻ ለማገልገል ፈቃደኛ የሆናችሁ ባለሙያዎች ለሕብረተሰቡ ይጠቅማል ወይም ሕብረተሰቡን ያስተምራል የምትሏቸውን አገልግሎቶች በመያዝ ወደ ቤተ ክርስቲያናች እንድትመጡ በአክብሮት እንጋብዛለን።
|

