Get Adobe Flash player
የአማርኛና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት: ... እሁድ ከጠዋቱ 2 ተኩል እስከ 5 ተኩል...
Amharic & Spritual Teachings: Sunday 8:30 AM - 11:30 AM ...
የአካዳሚ እርዳታና የወጣት ፕሮግራም: .... ቅዳሜ ከቀኑ 8 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት...
Tutoring & Mentoring Program: Saturday 2:00 PM - 6:00 PM...

MAY
23

ዓርብ

መርሐ፡ ግብር።

 
ስብከተ ወንጌል
  ዘወትር ረቡዕ እና ዓርብ
  ከምሽቱ 12፡30 (6:30 pm)
የቅዳሴ አገልግሎት
  ዘወትር እሁድ ከጧቱ 12፡00(6:00am)
  በ21-የእመቤታቸን ወርሃዊ በዓል
  በ24-የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ወርሃዊ በዓል
የነግህ ጸሎት (የኪዳን ጸሎት)
 ከልደታ እስከ ሥላሴ ከጧቱ
 11፡00 ሰዓት (5:00 am) ጀምሮ
የሰንበት ትምህርት ቤት መርሐ ግብር 
  ዘወትር እሁድ ከቀኑ
6፡00 – 9፡00 ሰዓት (12:00 – 3:00)PM
ቤተ ክርስቲያኒቱ ክፍት
የምትሆንባቸው ሰዓታት

ለጸሎትና ካህናትን ለማነጋገር ለሚመጡ
ምዕመናን ቤተ ክርስቲያናችን ቀኑን ሙሉ ክፍት ናት። 



(Amharic Font download)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። 

“ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፣ ለፍጥረትም ሁሉ ወንጌልን ስበኩ።” ማር ፲፮፤፲፭ 

እንኳን ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ድረ ገጽ በሰላም መጡ።

የርዕሰ አድባረት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ ዋና ከተማ መሐል ላይ ከስልሳ ሽህ ሰኩየር ጫማ በላይ ይዞታ ገዝታ ላላፉት ሃያ ዓመታት መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቷን እያከናወነች የምትገኝ ቤተ ክርሰቲያን ናት።

ቤተ ክርሰቲያናችን ከጊዜ ወደ ጊዜ በምታሳየው ለውጥ እነሆ ዛሬ በካህናትና በምዕመናን ብዛት እንዲሁም በመንፈሳዊና በማህበራዊ አገልግሎተች ስፋት በሰሜን አሜሪካ ውስጥ ከሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርሰቲያናት ውስጥ በግንባር ቀደምትነት የምትጠቀስ ቤተ ክርሰቲያን ለመሆን በቅታለች። 

ቤተ ክርስቲያናችን ምዕመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተው እረፍት እንዲያገኙና ክካህናት የምክር አገልግሎት እንዲያገኙ ሳምንቱን ሙሉ በሯ ክፍት የሆነች፣ ሥርዓተ ቅዳሴው፣ ማኅሌቱ፣ ሰዓታቱ እና ሌሎችም አገልግሎቶች ሳይቋረጡ ከዓመት እስከ ዓመት  የሚከናወንባት  ቤተ ክርሰቲያን ናት። 

ቤተ ክርስቲያናችን በእግዚአብሔር እርዳታ፣ በእመቤታችን አማላጅነት እንዲሁም በካህናትና በምዕመናን ጸሎት፤ በመንፈሳዊና በማህበራዊ አገልግሎት፣ በካህናትና በምዕመናን ቁጥር፣ በንብረትና በሀብት ብዛት አሁን ለደረሰችበት ደረጃ ደርሳለች። አሁንም ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ምንነት ለምዕራቡ ዓለም የሚያሳይ ታሪካዊ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ለመገንባት ጉዞ ጀምራለች።  

መንፈሳዊና ማሕበራዊ አገልግሎታችን እንዲሰፋፋ ሁላችሁም በጸሎታችሁ፣ በሙያችሁ፣ በገንዘባችሁ እንድትደግፉን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም ጥሪያችንን እያስተላለፍን፣ የተለያዩ መንፈሳዊ መልዕክቶች፣ የቤተ ክርስቲያናችንን ወቅታዊ ዘገባዎች፣ የተለያዩ ክፍሎች የሚሰጡትን አገልግሎቶች እና ሌሎችንም ጠቃሚ መልዕክቶች በዚህ ድረ ገጹ አማካኝነት እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።
(Amharic Font download)


አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለመቅደስ የሚሆን ቤትን ትሠራ ዘንድ መርጦሃልና ጠንክረህ ፈጽመው።
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 28 :10  

  Please  support the new Church Construction (Pledge Form, የቃል፡ መግቢያ፡ ቅጽ።  )
 

እንሆ ከርስቶስ ሞትን አሸንፎ ተነሥቷል !!

 

DSKMariam Live 

 

Winning Num 2013 
 
 
 
 
 
Featured News, Reports & Updates
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
What's New

Press Release: (መግለጫ)
 
 
በርዕሰ፡አድባራት ደብረ፡ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ፡ክርስቲያን እና ከደብረ፡ሰላም ቅድስት ማርያም የመረዳጃ እድር መሀል በተደረገዉ እርቀ ሰላም ከሁለቱም ወገን የተሠጠው  መግለጫ ::
 
 
 
 
 
 
 
 
 

 

Administration Documents 

 

Finacial Documents  
Report / News